የትብብር ስልጠና ውል / Cooperative Training Agreement

በአድማስ ዩኒቨርሲቲ እና የትብብር ስልጠና በሚሰጥ ድርጅት መካከል የተደረገ የትብብር ስልጠና ውል

ውል ሰጭ፡ አድማስ ዩኒቨርሲቲ

አድራሻ፡

  • ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቤት ቁጥር 1089 ስ.ቁጥር 0115508808/10
  • ምስራቅ ካምፓስ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የቤት ቁጥር አዲስ፤ ስ.ቁጥር 0116687142/0116687620/0116687965
  • መስቀል ካምፓስ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤት ቁጥር 119 ስ. ቁጥር 0115152069

ውል ተቀባይ ፡ ---------------------------------------------------------------------------

( የትብብር ስልጠናውን የሚሰጠው ድርጅት ስም)

አድራሻ ፡- ከተማ፡ --------------- ክፍለ ከተማ ፡ ----------------------------------- ወረዳ፡ -------- ስ.ቁጥር፡ ---------------------------------------------- በ ------------------------------------------ ስራ አስኪያጅነት/ኃላፊ የሚመራ (የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወይም ኃላፊ ወይም ተወካይ ስም) (ከዚህ ቀጥሎ አስልጣኙ ድርጅት) እና አድማስ ዩኒቨርሲቲ (ከዚህ ቀጥሎ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ተብሎ ይጠቀሳል) መካከል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የትብብር ስልጠና ለመስጠት የተደረሰ ውል፡፡

በዚህ ውል መሰረት አስልጣኝ ድርጅት እና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋሙ የሚከተሉትን ተግባራት ለማከናወን ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

  1. አስልጣኙ ድርጅት ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የትብብር ስልጠና ስልጣኞችን በ -------------------------------------------------------------------------------------------------- ሙያ ዘርፈ ተቀብሎ በ --------------------------------------------------------------------------- (የአሰልጣኙ ድርጅት ስም) በ ---------------------------------------------------------------------------------------------------------- (የቅርጫፍ ወይም የወርክሾፑ አድራሻ ከላይ ከተገለፀው የተለየ ከሆነ) ለየብቃት አሃዱ (Competence) በተቀመጠው የስልጠና ሰዓት ሰልጣኞች በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ውስጥ ከሚሰጠው ስልጠና ጉን ለጐን ለማስልጠን ተስማምቷል፡፡
  2. አስልጣኙ ለስልጠናው አመቺ የሆነና ፣ንጽህናው የተጠበቀ፣ ስፍራ ብቃት ያለው አስልጣኘ ወይም ተቆጣጣሪ ለስልጠናው የሚውሉ ፣መሣሪያዎች ፣ቁሳቁሶች እና እቃዎች ከላይ በቁጥር 1 ላይ በተገለፀው ቦታ ላይ ከክፍያ ነፃ በሆነ መልኩ ለማቅረብ ተስማምቷል፡፡
  3. አስለጣኙ ድርጅት ስልጠናው ከሙያ ስልጠናው ዓላማና ከስርዓተ ትምህርቱ የተጣጣመ መሆኑ እና የሰልጣኞችን አቅም ባገናዘበ መስጠቱን ያረጋግጣል፡፡
  4. አስልጣኙ ድርጅት ሰልጣኞችን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ውስጥ ከሚሰጠው የክፍል ውስጥ ስልጠና ጉን ለጐን ትብብር ስልጠናውን ስለሚወስዱ የስልጠና ሰዓቱን የማመቻቸትና እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ካጋጠማቸው በድርጅቱ መምሪያ መሰረት ጉደያቸውን እንዲፈጽሙ ፈቃድ ያመቻቻል፡፡
  5. ሰልጣኞቹ ስልጠናውን በአግባቡ ለመከታተል ቁርጠኛ መሆኑን ከአስልጣኞች ወይም ተቆጣጣሪዎች የሚሰጡ መምሪያዎች መፈፀም በድርጅቱ መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ልምምድ ማድረግና የድርጅቱን ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፡፡
  6. ሰልጣኞች በምንም ዓየነት መልኩ አስልጣኝ ድርጅቱን ጉዳት ላይ የሚጥል ተግባር ላይ አንዲሰሩ አይፈቅድም ሆን ብለው ወይም በዴንታቢስነት ጉዳት የሚያደርሱ ሰልጣኞች በአስልጣኝ ድርጅቱ እና በቴክኒክና ሙያ የትምህርትና ስልጠና ተቋም መካከል በሚደርስ ስምምነት መሰረተ ላደረሱት ጉዳት ተመጣጣኝ ክፍያ እንዳፈጽሙ ይደረጋል፡፡
  7. አስልጣኝ ድርጅት ሰልጣኞች ስልጠናውን አጠናቅቀው ሲመረቁ በድርጅቱ ውስጥ ለመቅጠር ቢፈልግ የሚያገኟቻውን ጥቅማቅሞች እና የቅጥሩ የቆይታ ጊዜ በዓመት ገልጾ በደብዳቤ ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡
  8. ይህ ውል በሦስት ኮፒዎች ተዘጋጅቶ የሁለቱም ወገኖች አንብበውት እና በጥልቀት ተረድተው የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች በተገኙበት ተፈርሟል፡፡
----------------------------------------------
የአስልጣኙ ድርጅት ስምና ፊርማ
----------------------------------------------
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም
በስልጠና ላይ ያሉ ድርጅቶች / Industries in Cooperative Training

No industries registered yet.

የትብብር ስልጠና ውል መሙያ እና መፈረሚያ ቅጽ / Sign as Industry
በሳጥኑ ውስጥ ይፈሩ ወይም በጽሁፍ ለመፈረም switch ያድርጉ።